የቢራቢሮ ክፍለመደብ
Appearance
የቢራቢሮ ክፍለመደብ (Lepidoptera) እጅግ ሰፊ የሦስት አጽቄ ክፍለመደብ ነው። ብዙ ዝርያዎች ለቁንጅናቸው ታውቀዋል።
ከበርካታ ዝርያዎቹ መካከል ብዙዎች ልብስን የሚበሉ አይነቶች ብል ይባላሉ። ሌሎች ቢራቢሮ ይባላሉ።
ቢራቢሮ በሕጻንነቱ በፍጹም የተለየ መልክ አለው፣ ይህም አባ ጨጓሬ ይባላል። እንደ አካለ መጠን ቢራቢሮ ከመሆኑ በፊት ምንም ክንፍ ወይም በረራ የለውም። ከጊዜ በኋላ አባ ጨጓሬ ሲያድግ በልቃቂት ወይም በምድር ተደብቆ ሙሽሬ ይሆናል፤ በኋላም ከዚህ ልቃቂት ወጥቶ አካለ መጠን የሚበርር ቢራቢሮ ነው።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |